የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሆሴዕ 3

3
ሆሴዕና አመንዝራይቱ ሴት
1እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “እስራኤላውያን ወደ ሌሎች አማልክት ሄደው የዘቢብ ጥፍጥፍ ማቅረብ ቢወዱ እንኳ ከዚሁ ጋር እግዚአብሔር ይወዳቸዋል፤ አንተም እንደዚሁ ፍቅረኛ ወደ አላት አመንዝራ ሴት ሄደህ ውደዳት።”
2ስለዚህ በዐሥራ አምስት ብርና በአንድ መቶ ኃምሳ ኪሎ ገብስ ገዛኋት፤ 3“ሳታመነዝሪና ሰውነትሽን ለማንኛውም ወንድ ሳትሰጪ እኔን እየጠበቅሽ ለብዙ ጊዜ መቈየት አለብሽ፤ እኔም ለአንቺ እንዲሁ አደርግልሻለሁ” ብዬ ነገርኳት። 4በዚሁ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ ወይም ያለ መሪ፥ ያለ መሥዋዕት ወይም ያለ ሐውልት፥ ያለ ልብሰ ተክህኖ ወይም የጣዖት ምስል ለብዙ ዘመን ይኖራሉ፤ 5ከዚህ ጊዜ በኋላ እስራኤላውያን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርና ወደ ንጉሣቸው ወደ ዳዊት ይመለሳሉ፥ በኋለኛው ዘመን በፍርሃት ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፤ በረከቱንም ይቀበላሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ