የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 6:17-18

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 6:17-18 አማ05

በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ውሳኔው የማይለወጥ መሆኑን ለማስረዳት ፈልጎ ለተስፋው ወራሾች ተስፋውን በመሐላ አጸናላቸው። በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።