የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 3:12-19

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 3:12-19 አማ05

ወዳጆቼ ሆይ፥ ከእናንተ መካከል ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያርቅ ክፉና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ። ይልቅስ ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ በየቀኑ ተመካከሩ። በመጀመሪያ የነበረንን እምነታችንን እስከ መጨረሻ አጽንተን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ወራሾች እንሆናለን። ይህም “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ በዚያ በዐመፃው ጊዜ እንዳደረጋችሁት ዐይነት ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ” ተብሎ እንደ ተነገረው ነው። ለመሆኑ እነዚያ ድምፁን ከሰሙ በኋላ ያመፁ እነማን ነበሩ? እነርሱ ሙሴ እየመራቸው ከግብጽ የወጡት ሁሉ አልነበሩምን? እግዚአብሔርን አርባ ዓመት ሙሉ ሲያስቈጡት የኖሩ እነማን ነበሩ? እነዚያ ኃጢአት የሠሩና ሬሳቸው በበረሓ ወድቆ የቀረው አይደሉምን? ደግሞስ እነዚያን ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር “ወደ ዕረፍቴ አትገቡም” ብሎ የማለባቸው እነማን ነበሩ? እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ባለማመናቸው ምክንያት መሆኑን እናያለን።