ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 3:1-6

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 3:1-6 አማ05

ስለዚህ ለሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ የተቀደሳችሁ ምእመናን ሆይ! የእምነታችን ሐዋርያና የካህናት አለቃ ኢየሱስን አስቡ። ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ታማኝ እንደ ነበረ ኢየሱስም ለሾመው ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበር። ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የበለጠ ክብር እንዳለው ሁሉ ኢየሱስም ከሙሴ ይልቅ የበለጠ ክብር ይገባዋል። በእርግጥ ለእያንዳንዱ ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉን ነገር የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው። ወደፊት መባል ለሚገባው ነገር ምስክር እንዲሆን ሙሴ በመላው በእግዚአብሔር ቤት እንደ አገልጋይ ታማኝ ነበር። ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።