አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል። ሁሉ ነገር በእርሱና ለእርሱ የተፈጠረው እግዚአብሔር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የመዳናቸውን መሪ ኢየሱስን በመከራ ፍጹም እንዲሆን እንዲያደርገው ተገባው። ሰዎችን ቅዱሳን የሚያደርጋቸውና በእርሱ ቅዱሳን የሆኑትም ሰዎች የአንድ አባት ልጆች ናቸው፤ በዚህ ምክንያት ኢየሱስ እነርሱን “ወንድሞቼ” ብሎ ለመጥራት አያፍርም። ስለዚህም በቅዱሳት መጻሕፍት “ስምህን ለወንድሞቼ አበሥራለሁ፤ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ” ይላል፤ እንዲሁም “እምነቴን በእርሱ ላይ እጥላለሁ” ይላል፤ እንደገናም “እነሆኝ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች እዚህ ነን” ይላል። ስለዚህ እነዚህ ልጆች ሥጋና ደም ያላቸው ሰዎች እንደ መሆናቸው ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሰው ሆነ፤ ይህን ያደረገውም በሞቱ አማካይነት በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስን ለማጥፋት ነው፤ እንዲሁም ሞትን በመፍራት ምክንያት ዕድሜ ልካቸውን በባርነት ይገዙ የነበሩትን ለመዋጀት ነው። የኢየሱስ ፍላጎት መላእክትን ሳይሆን የአብርሃምን ዘር ለመርዳት ነው፤ ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ። እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን መርዳት ይችላል።
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 2 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 2:9-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos