የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 2:5-9

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 2:5-9 አማ05

እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚመጣውን፥ ይህን የምንነጋገርበትን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም እንዲያውም በቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎአል፦ “አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ለእርሱስ ትጠነቀቅለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? ጥቂት ከመላእክት አሳነስከው፤ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፥ በእጆችህም ሥራ ላይ ሾምከው፤ ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አደረግህለት።” ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር ሲያደርግ፤ በሥልጣኑ ሥር ሳያደርግለት ያስቀረው ምንም ነገር የለም። ነገር ግን አሁን እንዳለ ሁሉ ነገር በእርሱ ሥልጣን ሥር እንደ ሆነ ገና አላየንም። አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል።