ታላቁን የበጎች እረኛ ጌታችንን ኢየሱስን በዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ደም ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ ፈቃዱን ለመፈጸም እንድትበቁ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሰኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለኢየሱስ ክርስቶስም ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ወንድሞች ሆይ! ይህ የጻፍኩላችሁ መልእክት አጭር ስለ ሆነ ይህን የምክር ቃሌን በትዕግሥት እንድትቀበሉ አጥብቄ እለምናችኋለሁ። ወንድማችን ጢሞቴዎስ ከእስር ቤት እንደ ወጣ እንድታውቁ እወዳለሁ፤ በቶሎ ወደዚህ ከመጣ ከእርሱ ጋር ወደ እናንተ መጥቼ አያችኋለሁ። ለመሪዎቻችሁና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ ከኢጣልያ መጥተው እዚህ ያሉት ክርስቲያኖች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:20-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች