ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:12-14

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 13:12-14 አማ05

እንዲሁም ኢየሱስ ሕዝቡን በገዛ ራሱ ደም ለመቀደስ ከከተማው በር ውጪ መከራን ተቀበለ። እኛም ከሰፈር ወጥተን ወደ እርሱ እንሂድ፤ የውርደቱም ተካፋዮች እንሁን። እኛ ገና የምትመጣውን ከተማ እንጠባበቃለን እንጂ ጸንታ የምትኖር ከተማ በዚህ ምድር የለችንም።