ከእርሱ ጋር የተስፋው ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በተስፋይቱ አገር መጻተኛ ሆኖ በድንኳን የኖረው በእምነት ነው። ይህንንም ያደረገው ጽኑ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር ያቀዳትንና የሠራትን ከተማ ይጠባበቅ ስለ ነበር ነው። ሣራም ተስፋ የሰጣት እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑን ስላወቀች ምንም እንኳ በዕድሜ በመግፋቷ መውለድ የማትችል ብትሆን የመፅነስን ኀይል ያገኘችው በእምነት ነው። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠረው ከአንዱ ከአብርሃም እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የማይቈጠር ዘር ተገኘ። እነዚህ ሁሉ በእምነት እንዳሉ ሞቱ፤ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውንም ነገር አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው ልክ እንዳገኙት አድርገው በደስታ ተቀበሉት። በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውንም ተገነዘቡ። እንዲህ የሚናገሩ ሰዎች የራሳቸው የሚሆነውን አገር እንደሚጠባበቁ በግልጽ ያመለክታሉ። ያንን የወጡበትን አገር አስታውሰውት ቢሆኑ ኖሮ ወደዚያ ለመመለስ በቻሉ ነበር። አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 11 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 11:9-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች