ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 10:36-39

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 10:36-39 አማ05

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማችሁ እግዚአብሔር ሊሰጣችሁ ቃል የገባላችሁን ነገር ለማግኘት በትዕግሥት መጠበቅ ያስፈልጋችኋል። ለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “ያ የሚመጣው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ አይዘገይምም፤ የእኔ የሆነ ጻድቁ ሰው ግን በእምነት ሕይወትን ያገኛል፤ ወደ ኋላው ቢያፈገፍግ ግን እኔ በእርሱ አልደሰትም።” እኛ ግን አምነው ከሚድኑት ወገን ነን እንጂ ወደ ኋላ አፈግፍገው ከሚጠፉት ሰዎች ወገን አይደለንም።