የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዕንባቆም 2:1-4

ትንቢተ ዕንባቆም 2:1-4 አማ05

በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ በግንቡ ጫፍ ላይም ቦታዬን እይዛለሁ፤ እግዚአብሔር ምን እንደሚለኝ ለጥያቄዬም ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “የምገልጥልህን ራእይ ጻፍ፤ በቀላሉ እንዲነበብም አድርገህ በሰሌዳ ላይ ቅረጸው፤ ምክንያቱም ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃል፤ እርሱም የሚናገረው የሚፈጸምበትን ቀን ነው፤ ሐሰትም የለበትም፤ ጊዜ የሚወስድ ቢመስልም ጠብቅ፤ በእርግጥ ይደርሳል፤ አይዘገይምም። ትዕቢተኞችን ተመልከት፤ አስተሳሰባቸው ቅን አይደለም፤ ጻድቃን ግን በእምነታቸው ይኖራሉ።”