እነሆ፥ ከሰማይ በታች ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት የጥፋት ውሃ አመጣለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ይጠፋል። ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ወደ መርከቡ ግቡ። “ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲጠበቁ ሥጋ ከለበሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ከየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየወሰድህ ወደ መርከቡ አስገባ፤ በሕይወት እንዲኖሩ ከየዐይነቱ ወፎች፥ ከየዐይነቱ እንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ከልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች በየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወደ አንተ ይምጡ። እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዐይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።” ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።
ኦሪት ዘፍጥረት 6 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 6:17-22
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች