ኦሪት ዘፍጥረት 50:18-21

ኦሪት ዘፍጥረት 50:18-21 አማ05

ከዚህ በኋላ ወንድሞቹ ራሳቸው በፊቱ ቀርበው ጐንበስ ብለው እጅ ነሡና “እነሆ እኛ ሁላችን አገልጋዮችህ ነን” አሉት። ነገር ግን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የምሆን አይደለሁም፤ በእርግጥ እናንተ ክፉ ነገር መክራችሁብኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ወደ መልካም ነገር ለወጠው፤ ይህንንም ያደረገው አሁን በሕይወት ያሉትን የብዙ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ብሎ ነው። ምንም የሚያስፈራችሁ ነገር የለም፤ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ።” በዚህም ዐይነት በመልካም ንግግር በማጽናናት አረጋጋቸው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}