ዘፍጥረት 50:18-21
ዘፍጥረት 50:18-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ፤ “እነሆ፥ እኛ ለአንተ አገልጋዮችህ ነን” አሉት። ዮሴፍም አላቸው፥ “አትፍሩ፤ ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖአልና። እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ። አሁንም አትፍሩ፤ እኔ እናንተንና ቤተ ሰቦቻችሁን እመግባችኋለሁ።” አጽናናቸውም፤ በልባቸው የሚገባ ነገርም ነገራቸው።
ዘፍጥረት 50:18-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም ወንድሞቹ መጡና በፊቱ ተደፍተው፣ “እኛ የአንተ ባሮች ነን” አሉት። ዮሴፍ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ እኔን በእግዚአብሔር ቦታ ማን አስቀመጠኝ? እናንተ እኔን ለመጕዳት ዐስባችሁ አድርጋችሁት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደሚታየው ሁሉ የብዙዎችን ሕይወት ለማዳን ለበጎ ነገር አዋለው። አሁንም ቢሆን አትፍሩ፤ ለእናንተና ለልጆቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” በማለት አረጋግጦ፣ በደግ ቃል አናገራቸው።
ዘፍጥረት 50:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው፦ እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን አሉት። ዮሴፍም አላቸው፦ አትፍሩ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን? እናንተ ክፋ ነገርን አሰባችሁብኝ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው። አሁንም አትፍሩ እኔ እናንተና ልጆቻችሁን እመግባችኍለሁ አጽናናቸውም ደስ አሰኛቸውም።
ዘፍጥረት 50:18-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ ወንድሞቹ ራሳቸው በፊቱ ቀርበው ጐንበስ ብለው እጅ ነሡና “እነሆ እኛ ሁላችን አገልጋዮችህ ነን” አሉት። ነገር ግን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የምሆን አይደለሁም፤ በእርግጥ እናንተ ክፉ ነገር መክራችሁብኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ወደ መልካም ነገር ለወጠው፤ ይህንንም ያደረገው አሁን በሕይወት ያሉትን የብዙ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ብሎ ነው። ምንም የሚያስፈራችሁ ነገር የለም፤ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ።” በዚህም ዐይነት በመልካም ንግግር በማጽናናት አረጋጋቸው።
ዘፍጥረት 50:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው፦ “እነሆ እኛ ለአንተ ባርያዎችህ ነን አሉት።” ዮሴፍም አላቸው፦ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የምሆን ነኝ? እናንተ ክፋ ነገርን አሰባችሁብኝ፥ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው። አሁንም አትፍሩ፥ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ።” አጽናናቸውም ደስ አሰኛቸውም።