ኦሪት ዘፍጥረት 3:6-10

ኦሪት ዘፍጥረት 3:6-10 አማ05

ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ። የሁለቱም ዐይኖች ተከፍተው እራቁታቸውን እንደ ሆኑ ተገነዘቡ፤ ስለዚህ የበለስ ቅጠሎችን አገናኝተው ሰፉና በማገልደም እርቃናቸውን ሸፈኑ። በመሸ ጊዜ፥ እግዚአብሔር አምላክ በአትክልቱ ቦታ ውስጥ ሲመላለስ ድምፁን ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱ እግዚአብሔር አምላክ እንዳያያቸው በዛፎች መካከል ተደበቁ። ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ጠርቶ “የት ነው ያለኸው?” ሲል ጠየቀው። አዳምም “በአትክልቱ ቦታ ውስጥ የአንተን ድምፅ ሰማሁ፤ እራቁቴንም ስለ ሆንኩ በመፍራት ተደበቅሁ” አለ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}