ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ እባቡን እንዲህ አለው፦ “ይህን በማድረግህ ከእንስሶችና ከአራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምክ ሁን፤ ከዛሬ ጀምሮ በደረትህ እየተሳብክ ሂድ፤ ዕድሜህን ሙሉ ዐፈር ብላ፤ በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።” ሴቲቱንም፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቀትሽን፥ በምትወልጂበትም ጊዜ የምጥ ሥቃይሽን አበዛሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል። ለእርሱም ታዛዥ ትሆኚአለሽ” አላት። አዳምንም እንዲህ አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘አትብላ’ ያልኩህን ፍሬ ከዛፉ ወስደህ ስለ በላህ፥ አንተ በፈጸምከው ክፉ ሥራ ምክንያት ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ምግብህን ከእርስዋ የምትበላው በብርቱ ድካም ነው። ምድር እሾኽና አሜከላ ታበቅላለች፤ አንተም የዱር ተክሎችን ትበላለህ። ወደ መጣህበት ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ፥ እንጀራህን በግንባርህ ላብ ትበላለህ።” ዐፈር ነህና፥ ወደ ዐፈርም ትመለሳለህ። አዳምም ሚስቱ ሕይወት ላላቸው ሰብአዊ ፍጡሮች ሁሉ እናት ስለ ሆነች “ሔዋን” የሚል ስም አወጣላት። እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሔዋን ከቆዳ ልብስ ሠርቶ አለበሳቸው።
ኦሪት ዘፍጥረት 3 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 3:14-21
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች