የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 25:27-32

ኦሪት ዘፍጥረት 25:27-32 አማ05

ሁለቱም ልጆች አደጉ፤ ዔሳው በዱር መዋል የሚወድ ብልኅ አዳኝ ሆነ፤ ያዕቆብ ግን በቤት መዋል የሚወድ ጭምት ሰው ነበር። ዔሳው እያደነ ሥጋ ያበላው ስለ ነበረ ይስሐቅ ዔሳውን ይወድ ነበር። ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤ ስለዚህም ያዕቆብን “ከዚህ ከቀይ ወጥ ስጠኝ” አለው። ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር። ያዕቆብም “መጀመሪያ ብኲርናህን ሽጥልኝ” አለው። ዔሳውም “እኔ በራብ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኲርና ምን ያደርግልኛል?” አለው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}