የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 2:1-7

ኦሪት ዘፍጥረት 2:1-7 አማ05

የሰማይና የምድር፥ በውስጣቸው ያሉትም ነገሮች ሁሉ አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተፈጸመ። እግዚአብሔር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ ያረፈው በዚህ ቀን ስለ ሆነ፥ ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም። የሰማይና የምድር አፈጣጠር እንዲህ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ፥ ዝናብን ባለማዝነቡና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ፥ በምድር ላይ ምንም ዐይነት ተክል አልነበረም፤ ምንም ዐይነት ቡቃያ አልበቀለም። ይሁን እንጂ፥ ከምድር ውስጥ ምንጭ ፈልቆ የብሱን ሁሉ ያጠጣ ነበር። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}