የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 17:3-8

ኦሪት ዘፍጥረት 17:3-8 አማ05

አብራም ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አደርግሃለሁ፤ የብዙ ሕዝቦች አባት ስለማደርግህም ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ አብራም መሆኑ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል። እጅግ ብዙ ሕዝቦች እስኪሆኑ ዘሮችህን አበዛቸዋለሁ፤ ከእነርሱም መካከል ነገሥታት የሚሆኑ ይገኛሉ። “በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ። አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}