ኦሪት ዘፍጥረት 17:1-5

ኦሪት ዘፍጥረት 17:1-5 አማ05

አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ዘርህንም እጅግ አበዛዋለሁ” አለው። አብራም ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አደርግሃለሁ፤ የብዙ ሕዝቦች አባት ስለማደርግህም ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ አብራም መሆኑ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}