የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 11:11-30

ኦሪት ዘፍጥረት 11:11-30 አማ05

አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ። አርፋክስድም 35 ዓመት ሲሆነው ሳላሕን ወለደ። ከዚህ በኋላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሳላሕ 30 ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ዔቦር 34 ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ፋሌቅ 30 ዓመት ሲሆነው ረዑን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ረዑ 32 ዓመት ሲሆነው ሰሩግን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሰሩግ 30 ዓመት ሲሆነው ናኮርን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችን ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ናኮር 29 ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 119 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ታራ 70 ዓመት ከሆነው በኋላ አብራምን፥ ናኮርንና ሃራንን ወለደ። የአብራም፥ የናኮርና የሃራን አባት የነበረው የታራ ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ ሃራን ሎጥን ወለደ፤ ሃራን አባቱ ታራ ገና በሕይወት ሳለ በተወለደባት ከተማ በኡር ሞተ፤ ኡር የምትገኘው በከለዳውያን ምድር ነበር። አብራም ሣራይን አገባ፤ ናኮር ደግሞ ሚልካን አገባ፤ እርስዋም ዪስካንን የወለደ የሃራን ልጅ ናት። ሣራይ መኻን በመሆንዋ ልጅ አልወለደችም ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}