በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። እግዚአብሔርም፥ ብርሃን መልካም መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔርም ብርሃንን ከጨለማ ለየ። እግዚአብሔር ብርሃኑን “ቀን” ብሎ ጠራው፤ ጨለማውንም “ሌሊት” ብሎ ሰየመው። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም አንድ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃውን ከውሃ የሚለይ ጠፈር ይሁን” አለ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ጠፈርን ፈጠረ፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉት ውሆች ይለያዩ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ፥ ሌሊቱም ነጋ፤ ሁለተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “የብሱ ግልጥ ሆኖ እንዲታይ ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ሁሉ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 1:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos