ወንድሞቼ ሆይ! እኔ የሰበክሁላችሁ ወንጌል ከሰው የተገኘ አለመሆኑን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። ይህን ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ ገለጠልኝ እንጂ ከማንም ሰው አልተቀበልኩትም፤ ወይም ማንም ሰው አላስተማረኝም። ቀድሞ የአይሁድ እምነት ተከታይ በነበርኩበት ጊዜ እንዴት እንደ ኖርኩ ሰምታችኋል፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ከመጠን በላይ እያሳደድኩ ለማጥፋት እጥር ነበር። የአይሁድን እምነት በመጠበቅ በዘመኔ ከነበሩት ከብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቼ ሁሉ እበልጥ ነበር፤ ስለ አባቶችም ወግ ከፍተኛ ቅናት ነበረኝ። ነገር ግን ከመወለዴ በፊት እግዚአብሔር መረጠኝ፤ በጸጋውም ጠራኝ። ለአሕዛብ ስለ ልጁ የምሥራቹን ቃል እንዳበሥር እግዚአብሔር ልጁን ሊገልጥልኝ በወደደ ጊዜ እኔ ከማንም ጋር አልተማከርኩም፤ ወይም ከእኔ በፊት ሐዋርያት የነበሩትን ለመገናኘት ወደ ኢየሩሳሌም አልሄድኩም፤ ነገር ግን አስቀድሜ ወደ ዐረብ አገር ሄድኩ፤ እንደገናም ወደ ደማስቆ ተመለስኩ። ቀጥሎም ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋ የሚባለውን ጴጥሮስን ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ፤ እዚያም ከእርሱ ጋር ዐሥራ አምስት ቀን ቈየሁ። የጌታን ወንድም ያዕቆብን አየሁ እንጂ ከሌሎቹ ከሐዋርያት ማንንም አላየሁም። ይህ የምጽፍላችሁ ሐሰት እንዳልሆነ በእግዚአብሔር ፊት አረጋግጥላችኋለሁ።
ወደ ገላትያ ሰዎች 1 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ገላትያ ሰዎች 1:11-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች