ትንቢተ ሕዝቅኤል 8:11-16

ትንቢተ ሕዝቅኤል 8:11-16 አማ05

የሻፋንን ልጅ አዛንያን ጨምሮ ሰባ የእስራኤላውያን መሪዎች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጥና ይዞ ነበር፤ ከጥናውም መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጢስ ይወጣ ነበር፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል መሪዎች በየራሳቸው ጣዖት ቤት በጨለማ ሆነው እግዚአብሔር አያየንም! ምድሪቱንም ትቶአታል በማለት የሚያደርጉትን ታያለህን?” አለኝ። እርሱም እንደገና “ከዚህም እንኳ የሚበልጥ አጸያፊ ነገር ሲያደርጉ ታያቸዋለህ” አለኝ፤ ስለዚህ በስተሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ ቅጽር በር ወሰደኝ፤ ተሙዝ ለተባለው ጣዖታቸው ሴቶች ሲያለቅሱለት አሳየኝ። እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ታያለህን? ገና ከዚህ የባሰ አጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ። ስለዚህ በውስጥ በኩል ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ወሰደኝ፤ እዚያም ወደ መቅደሱ መግቢያ አጠገብ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ኻያ አምስት ያኽል ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ጀርባቸውን ወደ መቅደሱ አድርገው የምትወጣዋን ፀሐይ በማምለክ ወደ ምሥራቅ ተንበርክከው ይሰግዱ ነበር።