ሕዝቅኤል 8:11-16 - Compare All Versions

ሕዝቅኤል 8:11-16 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በፊ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰባ ሰዎ​ችና የሳ​ፋን ልጅ ያእ​ዛ​ንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በእጁ ጥና​ውን ይዞ ነበር፥ የዕ​ጣ​ኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር። እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በስ​ውር እያ​ን​ዳ​ንዱ በሥ​ዕሉ ቤት የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አይ​ተ​ሃ​ልን? እነ​ርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​የ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን ትቶ​አ​ታል ይላ​ሉና” አለኝ። እር​ሱም፥ “ከዚያ የበ​ለ​ጠ​ውን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ታላቅ ኀጢ​አት ታይ ዘንድ ና” አለኝ። ወደ ሰሜ​ንም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም፥ ሴቶች ለተ​ሙዝ እያ​ለ​ቀሱ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር። እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አይ​ተ​ሃ​ልን? ደግሞ ከዚህ የበ​ለጠ ርኵ​ሰት ታያ​ለህ” አለኝ። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።

ሕዝቅኤል 8:11-16 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በእነዚህም ፊት ከእስራኤል ቤት ሰባ ሽማግሌዎች ቆመው ነበር፤ በመካከላቸውም የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆሞ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በእጃቸው ጥና ይዘዋል፤ መልካም መዐዛ ያለው የዕጣን ጢስም እየተትጐለጐለ ይወጣ ነበር። እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዳቸው በጣዖታቸው ምስል ጓዳ ውስጥ በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ፣ ‘እግዚአብሔር አያየንም፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቷል ይላሉ’ ” አለኝ። ደግሞም፣ “ከእነዚህ የባሰ አስጸያፊ ነገር ሲሠሩ ታያለህ” አለኝ። ከዚህም በኋላ በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ በዚያም ሴቶች ተቀምጠው ተሙዝ ለተባለው ጣዖት ሲያለቅሱ አየሁ። እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን አይተሃልን? ከዚህም የባሰ አስጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ። ደግሞም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ ሃያ ዐምስት ሰዎች ያህል ነበሩ፤ ጀርባቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አድርገው ለምትወጣዋ ፀሓይ ይሰግዱ ነበር።

ሕዝቅኤል 8:11-16 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በፊታቸውም ከእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች ሰባ ሰዎች ቆመው ነበር፥ በመካከላቸውም የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆሞ ነበር፥ ሰውም ሁሉ እያንዳንዱ በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ የዕጣኑም ጢስ ሽቱ ይወጣ ነበር። እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በጨለማ እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ፦ እግዚአብሔር አያየንም፥ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል ይላሉና አለኝ። እርሱም፦ ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠውን ያሚያደርጉትን ታላቅ ርኵሰት ታያለህ አለኝ። ወደ ሰሜንም ወደሚመለከተው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ እነሆም፥ ሴቶች ለተሙዝ እያለቀሱ በዚያ ተቀምጠው ነበር። እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ርኵሰት ታያለህ አለኝ። ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፥ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።

ሕዝቅኤል 8:11-16 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የሻፋንን ልጅ አዛንያን ጨምሮ ሰባ የእስራኤላውያን መሪዎች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጥና ይዞ ነበር፤ ከጥናውም መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጢስ ይወጣ ነበር፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል መሪዎች በየራሳቸው ጣዖት ቤት በጨለማ ሆነው እግዚአብሔር አያየንም! ምድሪቱንም ትቶአታል በማለት የሚያደርጉትን ታያለህን?” አለኝ። እርሱም እንደገና “ከዚህም እንኳ የሚበልጥ አጸያፊ ነገር ሲያደርጉ ታያቸዋለህ” አለኝ፤ ስለዚህ በስተሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ ቅጽር በር ወሰደኝ፤ ተሙዝ ለተባለው ጣዖታቸው ሴቶች ሲያለቅሱለት አሳየኝ። እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ታያለህን? ገና ከዚህ የባሰ አጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ። ስለዚህ በውስጥ በኩል ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ወሰደኝ፤ እዚያም ወደ መቅደሱ መግቢያ አጠገብ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ኻያ አምስት ያኽል ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ጀርባቸውን ወደ መቅደሱ አድርገው የምትወጣዋን ፀሐይ በማምለክ ወደ ምሥራቅ ተንበርክከው ይሰግዱ ነበር።

ሕዝቅኤል 8:11-16 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች ሰባ ሰዎች ቆመው ነበር፥ የሻፋን ልጅ ያአዛንያ በመካከላቸው ቆሞ ነበር፥ እያንዳንዱም በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ መልካም መዓዛ ያለው የዕጣኑም ጢስ ወደ ላይ ይወጣ ነበር። እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።” ደግሞም “ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኩሰት ሲያደርጉ ታያለህ” አለኝ። ወደ ሰሜንም ወደሚመለከተው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ እነሆ፥ ሴቶች ለታሙዝ እያለቀሱ በዚያ ተቀምጠው ነበር። እርሱም፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ርኩሰት ታያለህ” አለኝ። ወደ ጌታ ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በጌታ መቅደስ መግቢያ፥ በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት ያህል ሰዎች ነበሩ፥ ጀርባቸው ወደ ጌታ መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፥ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።