ትንቢተ ሕዝቅኤል 36:26-27

ትንቢተ ሕዝቅኤል 36:26-27 አማ05

አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ ከሰውነታችሁ እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣችኋለሁ። መንፈሴን አሳድርባችኋለሁ፤ የሰጠኋችሁንም ሕግና ሥርዓት ሁሉ በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችሉ አደርጋችኋለሁ።