እርሱም በዕብራይስጥ ሀዳሳ የተባለችውን የአጐቱን ልጅ አስቴርን ያሳድግ ነበር፤ እርስዋም ቁመናዋ የተስተካከለ እጅግ ውብ ልጃገረድ ነበረች፤ ወላጆችዋም ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ መርዶክዮስ ወደ ቤቱ በመውሰድ ልክ እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ በመንከባከብ አሳደጋት። ንጉሡ ዐዋጁን ባስተላለፈ ጊዜ ወደ ሱሳ ከተማ ከመጡት ብዙ ልጃገረዶች መካከል አንድዋ አስቴር ነበረች፤ እርስዋም ወደ ቤተ መንግሥት ተወስዳ የምርጥ ሴቶች መኖሪያ ቤት ኀላፊ በሆነው በሄጋይ ቊጥጥር ሥር እንድትሆን ተደረገ። አስቴርም ሄጋይን ደስ አሰኘችው፤ በፊቱም ሞገስ አገኘች፤ ጊዜም ሳያባክን ወዲያውኑ ጥሩ ምግብ እንዲሰጣትና የሰውነትዋ ቅርጽ በመታሸት እንዲስተካከል በማድረግ በቊንጅና እንክብካቤ እንድትጠበቅ ወሰነ፤ ከምርጥ ሴቶችም መኖሪያ ቤት ከሁሉ የተሻለውን ክፍል መርጦ በመስጠት ከቤተ መንግሥት የተመረጡ ሰባት ደንገጡሮች ያገለግሉአት ዘንድ መደበላት።
መጽሐፈ አስቴር 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ አስቴር 2:7-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች