ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:21-25

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:21-25 አማ05

ለክርስቶስ ክብር ብላችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ለሌላው ይታዘዝ። ሚስቶች ሆይ! ለጌታ ኢየሱስ እንደምትታዘዙ ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ባልም የሚስቱ ራስ ነው፤ ደግሞም ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን አዳኝዋ ነው። ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትታዘዝ እንዲሁም ሚስቶች በሁሉ ነገር ለባሎቻቸው ይታዘዙ። ባሎች ሆይ! ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳትና ራሱንም ስለ እርስዋ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤