የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳግም 6:4-9

ኦሪት ዘዳግም 6:4-9 አማ05

“እስራኤል ሆይ! ይህን አስታውስ! እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኀይልህ ውደድ፤ ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች አትርሳ፤ እነዚህኑ ትእዛዞች ለልጆችህ አስተምራቸው፤ በቤት ስትቀመጥም ሆነ በመንገድ ስትሄድ፥ ዕረፍት በምታደርግበትም ጊዜ ሆነ ሥራ በምትሠራበት ጊዜ ሁሉ፥ እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር አሰላስል፤ ምልክት ይሆኑህ ዘንድ በእጅህ ላይ እሰራቸው፤ በግንባርህም እንደ መለያ ለጥፋቸው። በቤትህ ደጃፍ መቃኖችና በቅጽር በሮችህ ላይ ጻፋቸው።