ኢዮአቄም በይሁዳ ላይ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት። እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ። ከዚህ በኋላ ንጉሥ ናቡከደነፆር አሽፈናዝ የተባለውን የባለሟሎቹን አለቃ ከእስራኤል ምርኮኞች መካከል የንጉሣዊ ቤተሰቦችና የመሳፍንት ልጆች ከሆኑት ወጣቶች መካከል ጥቂቶቹን መርጦ እንዲያመጣ አዘዘው፤ የሚመረጡትም ወጣቶች በቤተ መንግሥት ለማገልገል በቂ ችሎታ እንዲኖራቸው፥ መልከ መልካሞች፥ ጥበብን ሁሉ ማስተዋልና ሁሉን ነገር በፍጥነት መረዳት የሚችሉ፥ የአካል ጒድለት የሌለባቸው መሆን ይገባቸዋል፤ እንዲሁም የባቢሎናውያንን ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ያስተምራቸውም ዘንድ አዘዘው። ምግባቸውና የሚጠጡት የወይን ጠጅ ከንጉሡ ማእድ እንዲሆን ታዘዘላቸው፤ በዚህ ዐይነት ለሦስት ዓመት ከሠለጠኑ በኋላ በንጉሡ ፊት ቀርበው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ተወሰነ። ከተመረጡትም መካከል ነገዳቸው ከይሁዳ ወገን የሆነ ዳንኤል፥ ሐናንያ፥ ሚሳኤልና ዐዛርያ ነበሩ። የንጉሡም ባለሟሎች አለቃ ስማቸውን በመለወጥ ዳንኤልን ብልጣሶር፤ ሐናንያን ሲድራቅ፤ ሚሳኤልን ሚሳቅ፤ ዐዛርያን አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።
ትንቢተ ዳንኤል 1 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ዳንኤል 1:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos