ትንቢተ አሞጽ መግቢያ
መግቢያ
አሞጽ የትንቢት ሙያ አልነበረውም፤ ትንቢት በመናገር ሙያም አልሠለጠነም (ም. 7፥14)። ነገር ግን ጌታ በሰሜኑ መንግሥት ውስጥ ለሚገኝ ሕዝብ መልእክት እንዲያደርስ በላከው ጊዜ አሞጽ በይሁዳ የምትገኘዋን ተቆዓ የምትባለዋን መንደሩን ትቶ ሄደ። ከዚያም ተነሥቶ የእስራኤላውያን ዝነኛ የአምልኮ ቦታ ወደ ነበረችው ወደ ቤቴል ከተማ ሄደ።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አሞጽ በመጀመሪያ የአካባቢ ሕዝቦችን ያወግዛል፤ ከዚያም የእስራኤልን ሕዝብ በተለይም የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖሩ ሐብታሞችን ያወግዛል። እነርሱ ሕዝቡን ለመዝረፍና ባሪያ አድርጎ ለመግዛት ታላቅ ኀይል ነበራቸው። ብዙዎቻቸው ከጌታ ሌላ የሚያመልኳቸው አማልክት ቢኖሩአቸውም እንኳ እግዚአብሔር እንደሚጠብቃቸው ተስፋ ያደርጉ ነበር። አሞጽ ግን እንዲህ በማለት በኃጢአታቸው እንደሚቀጡ ነገራቸው፦
“ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካም የሆነውን ነገር ውደዱ።
በየፍርድ አደባባዩም ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለተረፉት የእስራኤል ሕዝብ ምሕረት ያደርግላቸው ይሆናል።” (5፥15)
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. ሕዝቦች በወንጀላቸው እንደሚቀጡ (1፥1—3፥2)
2. የእስራኤልና የሰማርያ ጥፋት (3፥3—6፥14)
3. ስለ እስራኤል ቅጣት አሞጽ ያያቸው አምስት ራእዮች (7፥1—9፥10)
4. የእስራኤል ብሩህ ተስፋ (9፥11-15)
Currently Selected:
ትንቢተ አሞጽ መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997