በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል መቀበላቸውን በሰሙ ጊዜ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ሰማርያ ላኩአቸው። ስለዚህ የሰማርያ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሄደው ጸለዩላቸው። የሰማርያ ሰዎች በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠምቀው ነበር እንጂ መንፈስ ቅዱስ ገና በአንዳቸውም ላይ አልወረደም ነበር። ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ፥ እጆቻቸውን በጫኑባቸው ጊዜ ሰዎቹ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። ሐዋርያት እጆቻቸውን ሲጭኑባቸው መንፈስ ቅዱስ ለሰዎቹ መሰጠቱን ስምዖን ባየ ጊዜ ገንዘብ አመጣላቸውና፥ “እኔም እጄን የምጭንበት ሰው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል ይህን ሥልጣን ስጡኝ” አለ። ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት በማሰብህ ገንዘብህ ካንተ ጋር ይጥፋ! ልብህ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ስላልሆነ አንተ ከዚህ ነገር ክፍል ወይም ዕጣ የለህም። እንግዲህ ከዚህ ከክፋትህ ተጸጽተህ ንስሓ ግባ፤ ምናልባት የልብህን ክፉ አሳብ ይቅር ይልልህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ለምን። አንተ በመራራ ቅናት እንደ ተሞላህና የኃጢአት እስረኛ እንደ ሆንክ አያለሁ።” ስምዖንም “አሁን ከተናገራችሁት አንዳች እንኳን እንዳይደርስብኝ እናንተው ራሳችሁ ወደ ጌታ ጸልዩልኝ” አላቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ ከመሰከሩና የጌታንም ቃል ከተናገሩ በኋላ በብዙ የሰማርያ መንደሮች ወንጌልን እያበሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
የሐዋርያት ሥራ 8 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሐዋርያት ሥራ 8:14-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች