የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐዋርያት ሥራ 28:7-10

የሐዋርያት ሥራ 28:7-10 አማ05

በዚያ በነበርንበት ስፍራ አጠገብ የደሴቲቱ ገዢ የፑፕልዮስ መሬት ነበር፤ ይህ ሰው በቤቱ ተቀብሎን ሦስት ቀን በጥሩ ሁኔታ አስተናገደን። በዚያን ጊዜ የፑፕልዮስ አባት ትኩሳትና ተቅማጥ ይዞት ታሞ ተኝቶ ነበር፤ ጳውሎስ ወደ እርሱ ገብቶ ጸለየለት፤ እጁንም ጫነበትና ፈወሰው። ይህ ከሆነ በኋላ በደሴቲቱ የሚኖሩት ሌሎች በሽተኞች መጡና ተፈወሱ። ሰዎቹ ብዙ ስጦታ አመጡልን፤ አክብሮታቸውንም ገለጡልን፤ በመርከብ ለመሄድ በተነሣንም ጊዜ የሚያስፈልገንን ሁሉ በመርከብ ላይ ጫኑልን።