የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐዋርያት ሥራ 24:22-27

የሐዋርያት ሥራ 24:22-27 አማ05

ፊልክስ ግን ስለ ክርስትና እምነት በደንብ ያውቅ ስለ ነበር “የጦር አዛዡ ሉስዮስ በመጣ ጊዜ፥ ስለ ጉዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ አሰናበታቸው። ጳውሎስን ይጠብቅ የነበረውንም መቶ አለቃ “እምብዛም ነጻነት ሳትከለክለው በጥንቃቄ ጠብቀው፤ ወዳጆቹም የሚያስፈልገውን ሁሉ ይዘውለት ሲመጡ አትከልክልበት” አለው። ከጥቂት ቀኖች በኋላ ፊልክስ ዱሩሲላ ከተባለች አይሁዳዊት ሚስቱ ጋር መጣ፤ ጳውሎስንም አስጠርቶ በኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ማመን ሲናገር ሰማ። ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በተናገረ ጊዜ ፊልክስ ፈርቶ “አሁን ሂድ፤ ሲመቸኝ ሌላ ጊዜ አስጠራሃለሁ” አለው። ፊልክስ ከጳውሎስ ጉቦ ለመቀበል ተስፋ ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ ብዙ ጊዜ ጳውሎስን እያስጠራ ያነጋግረው ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ቦታ ተተካ፤ ፊልክስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ፈልጎ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።