የሐዋርያት ሥራ 2:44-47

የሐዋርያት ሥራ 2:44-47 አማ05

አማኞች ሁሉ በአንድነት አብረው ይኖሩ ነበር፤ ያላቸውም ነገር ሁሉ የጋራ ነበር። ዕርሻቸውንና ሀብታቸውን እየሸጡ ገንዘቡን ለእያንዳንዱ እንደሚያስፈልገው ያከፋፍሉ ነበር። በየቀኑ በቤተ መቅደስ በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር፤ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ በደስታና በጥሩ ልብ ይመገቡ ነበር፤ ጌታንም ያመሰግኑ ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያከብራቸው ነበር፤ እግዚአብሔርም የሚድኑትን ሰዎች በየቀኑ ወደ ማኅበራቸው ይጨምር ነበር።