የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐዋርያት ሥራ 17:10-12

የሐዋርያት ሥራ 17:10-12 አማ05

ወንድሞች በቶሎ ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ እንዲሄዱ አደረጉአቸው፤ እዚያም በደረሱ ጊዜ ወደ አይሁድ ምኲራብ ገቡ። በቤርያ ያሉት አይሁድ በተሰሎንቄ ካሉት ይልቅ ቅን አመለካከት ያላቸው ስለ ነበሩ ቃሉን በታላቅ ደስታ ተቀበሉ፤ የቃሉንም እውነተኛነት ለማረጋገጥ በየቀኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይመረምሩ ነበር። ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎች አመኑ፤ ብዙዎች የግሪክ ሀብታሞች ሴቶችና ብዙዎች ግሪካውያን ወንዶችም አመኑ።