የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐዋርያት ሥራ 16:11-15

የሐዋርያት ሥራ 16:11-15 አማ05

ከጢሮአዳ በመርከብ ተሳፍረን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ ሄድን፤ በማግስቱም ወደ ናጱሌ ሄድን። ከዚያም ተነሥተን ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ ፊልጵስዩስ በመቄዶንያ የምትገኝ ታላቅ ከተማና የሮማውያን ቅኝ አገር ነበረች፤ በዚህችም ከተማ ጥቂት ቀኖች አሳለፍን። በሰንበትም ቀን ለጸሎት ይሰበሰቡበት ወደነበረው ከከተማው ውጪ ወደሚገኘው ወደ ወንዝ ዳር ሄድን፤ እዚያም ተቀምጠን ለተሰበሰቡት ሴቶች የእግዚአብሔርን ቃል አስተማርን። ይሰሙን ከነበሩትም ሴቶች አንድዋ የትያጥሮን ከተማ ተወላጅ የሆነች የቀይ ልብስ ነጋዴ፥ ልድያ የምትባል ሴት ነበረች፤ እርስዋ እግዚአብሔርን የምታመልክ ሴት ነበረች፤ ጌታም ልቡናዋን ስለ ከፈተላት ጳውሎስ የሚናገረውን ቃል ታዳምጥ ነበር፤ እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።