2 ተሰሎንቄ ሰዎች 3:1-5

2 ተሰሎንቄ ሰዎች 3:1-5 አማ05

በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ዘንድ እንደሆነው ሁሉ የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲስፋፋና እንዲከበር ለእኛ ጸልዩልን፤ እንዲሁም ቃሉን የሰሙት ሁሉ የሚያምኑ አይደሉም፤ ስለዚህ ከጠማሞችና ከክፉ ሰዎች እንድንድን ጸልዩልን። ጌታ ግን ታማኝ ነው፤ እርሱ ያበረታችኋል፤ ከሰይጣንም ይጠብቃችኋል፤ የምናዛችሁን አሁንም ሆነ ወደፊት እንደምትፈጽሙት በጌታ እንተማመንባችኋለን። ጌታ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ትዕግሥት ይምራው።