ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት መግቢያ
መግቢያ
መጽሐፈ ነገሥት ክፍል ሁለት፥ መጽሐፈ ነገሥት ክፍል አንድ ካቆመበት በመነሣት ስለ ሁለቱ የእስራኤል መንግሥታት ይተርካል፤ መጽሐፉ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ሊመደብ ይችላል፦
1. ከክርስቶስ ልደት በፊት ከዘጠነኛው ምእት ዓመት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ሰማርያ መፍረስና ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰባት መቶ ኻያ አንድ ዓመት እስከ ሰሜናዊው መንግሥት መውደቅ ድረስ የነበረው የሁለቱ መንግሥታት ታሪክ፤
2. ከእስራኤል መንግሥት መውደቅ አንሥቶ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ዓመት ንጉሥ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን ይዞ እስካፈራረሳት ድረስ የነበረው የይሁዳ መንግሥት ታሪክ፤
መጽሐፉ ገዳልያ በባቢሎን አገዛዝ ሥር የይሁዳ አገረ ገዢ ስለ መሆኑና የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በባቢሎን ከእስር ቤት ስለ መውጣቱ በመተንተን ታሪኩን ይደመድማል።
ይህ ሁሉ ጥፋት በእስራኤል ላይ ሊመጣ የቻለው የይሁዳና የእስራኤል ነገሥታትና ሕዝብ ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት በማጓደላቸው ነው፤ የኢየሩሳሌም መፍረስና ከይሁዳም ሕዝብ መካከል አብዛኛው መሰደዱ የእስራኤላውያንን የታሪክ አቅጣጫ ሊለውጡ ከቻሉት ምክንያቶች ዋናው ነው።
በመጽሐፈ ነገሥት ክፍል ሁለት ውስጥ በጣም ታዋቂው ነቢይ የኤልያስ ተተኪ የነበረው ኤልሳዕ ነው።
የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት
የተከፋፈለው መንግሥት 1፥1—17፥41
ሀ. ነቢዩ ኤልያስ 1፥1—8፥15
ለ. የይሁዳና የእስራኤል ነገሥታት 8፥16—17፥4
ሐ. የሰማርያ አወዳደቅ 17፥5-41
የይሁዳ መንግሥት 18፥1—25፥30
ሀ. ከሕዝቅያስ እስከ ኢዮስያስ 18፥1—21፥26
ለ. የኢዮስያስ አገዛዝ 22፥1—23፥30
ሐ. የመጨረሻዎቹ የይሁዳ ነገሥታት 23፥31—24፥20
መ. የኢየሩሳሌም አወዳደቅ 25፥1-30
Currently Selected:
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997