የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:12-18

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:12-18 አማ05

እንዲህ ዐይነቱ ተስፋ ስላለን በድፍረት እንናገራለን። ሙሴ እየከሰመ የሚሄደው የፊቱ መንጸባረቅ እስኪወገድ ድረስ እስራኤላውያን እንዳያዩ ፊቱን ይሸፍን ነበር፤ እኛ ግን እንደ እርሱ አይደለንም። የእነርሱ ልቡና በእርግጥ ደንዝዞአል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ሲያነብቡ ልቡናቸው በዚያው መሸፈኛ እንደ ተሸፈነ ነው። ይህም የሚሆነው ያ መሸፈኛ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ስለ ሆነ ነው። ዛሬም እንኳ ቢሆን የሕግ መጻሕፍትን ባነበቡ ቊጥር ልቡናቸው በመሸፈኛው ይሸፈናል። ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ሲመለስ “መሸፈኛው ይወገዳል።” ጌታ መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት ነጻነት አለ። እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።