ሰውን ያሳዘነ ማንም ቢኖር ያሳዘነው እኔን ሳይሆን በደሉን ማጋነን አይሁንብኝ እንጂ በሌላ በኩል ከእናንተ ብዙዎቹን አሳዝኖአል። ለእንዲህ ዐይነቱ ሰው ከእናንተ አብዛኞቹ የፈረዱበት ቅጣት ይበቃዋል። ስለዚህ ይህ ሰው በጣም ከማዘኑ የተነሣ ተስፋ እንዳይቈርጥ ይልቅስ ይቅርታ እንድታደርጉለትና እንድታጽናኑት ይገባል። እንዲሁም እርሱን የምትወዱት መሆናችሁን እንደገና እንድታረጋግጡለት እለምናችኋለሁ። ያንንም መልእክት የጻፍኩላችሁ ተፈትናችሁ በሁሉ ነገር ታዛዦች መሆናችሁን ለመረዳት ብዬ ነው። እናንተ ይቅርታ ለምታደርጉለት ሰው እኔም ይቅርታ አደርግለታለሁ፤ ይቅር የምልለት በደል ካለ እኔ በክርስቶስ ፊት ይቅርታ የማደርግለት ስለ እናንተ ብዬ ነው። ይህንንም የማደርገው የሰይጣንን የተንኰል ሥራ ስለምናውቅ ሰይጣን እንዳያታልለን ብዬ ነው።
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:5-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos