የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:7-10

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:7-10 አማ05

ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል። ይህ የሚያሠቃየኝ ነገር ከእኔ እንዲወገድልኝ ጌታን ሦስት ጊዜ ለመንኩት። ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ። ኀይል የማገኘው ደካማ በምሆንበት ጊዜ ስለ ሆነ ስለ ክርስቶስ ስደክም፥ ስሰደብ፥ ስቸገር፥ ስሰደድ፥ ስጨነቅ ደስ ይለኛል።