የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 8

8
ሰሎሞን ያከናወናቸው ሌሎች ሥራዎች
(1ነገ. 9፥10-28)
1ሰሎሞን ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት ኻያ ዓመት ፈጀበት፤ 2እንዲሁም ንጉሥ ኪራም የሰጠውን ከተሞች እንደገና ሠርቶ እስራኤላውያን እንዲሰፍሩባቸው አደረገ፤ 3ሰሎሞን በሐማትና በጾባ ግዛቶች ላይ ዘምቶ በቊጥጥሩ ሥር አደረጋቸው፤ 4በበረሓ የምትገኘውን የታጽሞርን ከተማና በሐማት ያለውን የስንቅና የትጥቅ ማኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ አጠናከረ፤ 5እንዲሁም ሰሎሞን በላይኛውና በታችኛው ቤትሖሮን በብረት መዝጊያ ሊዘጉ የሚችሉ ቅጽር በሮች ያሉአቸው የተመሸጉ ከተሞችን እንደገና ሠራ፤ 6የባዕላት ከተማ፥ ስንቅና ትጥቅ የሚያስቀምጥባቸው ከተሞች ሁሉ፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚኖሩባቸው ከተሞች፤ በዚህም ዐይነት ሰሎሞን በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በእርሱ አስተዳደር ባለው ግዛት በሙሉ ሊሠራ ያቀዳቸውን የግንባታ ሥራዎች ሁሉ ፈጸመ። 7-8ሰሎሞን በጒልበት ሥራ ያሰማራቸው ገባሮች፥ እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በያዙ ጊዜ ያልገደሉአቸው የከነዓን ሕዝብ ዘሮች ነበሩ፤ እነዚህም የከነዓን ዘሮች እስከ አሁን ድረስ ባሪያዎች ሆነው የሚያገለግሉ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ናቸው፤ 9ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ እስራኤላውያን ወታደሮች፥ የጦር መኰንኖች፥ የጦር አዛዦች፥ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኀላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር። 10ሰሎሞን ለሚያከናውነው ልዩ ልዩ የሕንጻ ሥራ፥ የጒልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ገባሮች ሁለት መቶ ኀምሳ እስራኤላውያን ኀላፊዎች ነበሩአቸው።
11ሰሎሞን “የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ያለበት ስፍራ ሁሉ ቅዱስ ስለ ሆነ፥ ግብጻዊት ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤተ መንግሥት ውስጥ መኖር አይገባትም” በማለት የግብጽ ንጉሥ ልጅ የሆነችውን ሚስቱን ከዳዊት ከተማ አውጥቶ እርሱ ወዳሠራላት ወደ ሌላ መኖሪያ ቤት ተዘዋውራ እንድትኖር አደረገ።
12ሰሎሞን በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ባሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ 13ሙሴ ባዘዘው መሠረትም በእያንዳንዱ የበዓል ቀን ማለትም በየሰንበቱ፥ በየወሩ መባቻ፥ በየዓመቱ በሚከበሩ ሦስት በዓላት ማለትም በቂጣ በዓል፥ በመከር በዓልና በዳስ በዓል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀርብ ነበር። #ዘፀ. 23፥14-17፤ 34፥22-23፤ ዘኍ. 28፥9፤ 29፥39፤ ዘዳ. 16፥16። 14አባቱ ዳዊት የደነገጋቸውን መመሪያዎች በመከተልም የካህናቱንና ካህናቱን በሥራና መዝሙር በመዘመር የሚረዱትን ሌዋውያን የየዕለቱን የሥራ መደብ አቀናበረ፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የቤተ መቅደሱ ዘበኞች በእያንዳንዱ ቅጽር በር የዕለት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አከፋፍሎ መደበ። 15እነርሱም ስለ ግምጃ ቤቶችና ስለ ሌሎችም ጉዳዮች ዳዊት ለካህናትና ለሌዋውያን በሰጠው መመሪያ መሠረት አንድም ሳይቀር ሁሉም በሚገባ እንዲከናወን አደረጉ።
16በዚህም ጊዜ የሰሎሞን የሥራ ዕቅድ ሁሉ፥ ማለትም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት መጣል ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ ሥራው ሁሉ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ።
17ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በኤዶም ምድር የባሕር ወደብ ወደሆኑት ወደ ዔጽዮንጋብርና ወደ ኤላት ሄደ፤ 18ንጉሥ ኪራም በሠለጠኑ መርከበኞች የሚነዱና በራሱ መኰንኖች የሚመሩ መርከቦችን ለሰሎሞን ልኮለት ነበር፤ እነርሱም ከሰሎሞን መኰንኖች ጋር በመሆን ወደ ኦፊር ምድር መጡ፤ ከዚያም ከዐሥራ አምስት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ ለሰሎሞን ይዘውለት መጡ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ