የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:14-19

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:14-19 አማ05

በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሕዝቡ ጋር በነበረ በአንድ ሌዋዊ ላይ ወረደ፤ ይህም ሌዋዊ ያሐዚኤል ተብሎ የሚጠራ የዘካርያስ ልጅ ነበር፤ እርሱም በማታንያ፥ በይዒኤልና በበናያ በኩል ደግሞ የአሳፍ ወገን ነበር፤ ያሐዚኤልም እንዲህ አለ፦ “ንጉሥ ሆይ! እናንተም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በሙሉ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ተስፋ አትቊረጡ፤ ይህንንም ታላቅ ሠራዊት ለመቋቋም አትፍሩ፤ ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለም፤ ስለዚህ ነገ እነርሱ በጺጽ አጠገብ ወዳለው መተላለፊያ ሲመጡ አደጋ ጣሉባቸው፤ በይሩኤል አጠገብ ወዳለው በረሓማ አገር በሚያመራው ሸለቆ መጨረሻ ጫፍ ላይ ታገኙአቸዋላችሁ። በዚህ ጦርነት ላይ የምትዋጉ እናንተ አይደላችሁም፤ ስፍራ ስፍራችሁን ይዛችሁ ብቻ ጠብቁ፤ እግዚአብሔር ድልን እንደሚያጐናጽፋችሁ ታያላችሁ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! ሳታመነቱና በፍርሃት ሳትሸበሩ ነገ በቀጥታ ሄዳችሁ ተዋጉ! እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል!’ ” ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና ከእርሱ ጋር የነበሩት የይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ የቀዓትና የቆሬ ጐሣዎች አባላት የሆኑ ሌዋውያን ቆሙ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።