ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 15:1-2

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 15:1-2 አማ05

የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በዐዛርያስ ላይ ወረደ፤ ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤