1 ወደ ጢሞቴዎስ 4:1-5

1 ወደ ጢሞቴዎስ 4:1-5 አማ05

መንፈስ ቅዱስ ግን በግልጥ እንዲህ ይላል፤ “በኋለኛው ዘመን አንዳንድ ሰዎች አሳሳች መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት በመከተል ሃይማኖትን ይክዳሉ።” እንዲህም ዐይነቱ ትምህርት የሚመነጨው በግብዝነት፥ ሐሰትን ሲናገሩ በጋለ ብረት እንደ ተተኮሰ ያኽል ሆኖ የደነዘዘ ኅሊናቸው ከማይወቅሳቸው ሰዎች ነው። እንደእነዚህ ያሉት ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎችም እርሱን እያመሰገኑ እንዲመገቡት እግዚአብሔር የፈጠረላቸውን ምግብ “አትብሉ” እያሉ ይከለክላሉ። ዳሩ ግን እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ መልካም ነው፤ በምስጋና ከተቀበሉት ምንም የሚጣል ነገር የለም። በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ይሆናል።