እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤ እግዚአብሔር የጠራን ለቊጣ ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት መዳንን እንድናገኝ ነው። ክርስቶስ ስለ እኛ የሞተው በሕይወት ብንሆን ወይም ብንሞት ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው። ስለዚህ አሁን በምታደርጉት ዐይነት አንዱ ሌላውን በማነጽ ያበረታታው። ወንድሞች ሆይ! በእናንተ መካከል በሥራ የሚደክሙትን፥ በጌታ ኢየሱስ አለቆቻችሁንና መካሪዎቻችሁ የሆኑትን እንድታከብሩአቸው እንለምናችኋለን፤ በሥራቸው ምክንያትም ለእነርሱ ታላቅ አክብሮትና ፍቅር ይኑራችሁ፤ እናንተም እርስ በርሳችሁ በሰላም ኑሩ። ወንድሞች ሆይ! “ሰነፎችን ገሥጹ፤ ፈሪዎችን አደፋፍሩ፤ ደካሞችን እርዱ፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ” ብለን እንመክራችኋለን። ማንም ሰው በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ይልቅስ ሁልጊዜ እናንተ ለእርስ በርሳችሁም ሆነ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም ለማድረግ ትጉ። ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ባለማቋረጥ ጸልዩ፤ በሁሉ ነገር እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ሕይወት እግዚአብሔር ከእናንተ የሚፈልገው ይህን ነው። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ አታዳፍኑ፤ የትንቢትን ስጦታ አትናቁ፤ ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ። ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ። ራሱ የሰላም አምላክ በሁሉ ነገር ይቀድሳችሁ፤ መንፈሳችሁ፥ ነፍሳችሁ፥ አካላችሁ በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚመጣበት ቀን ያለ ነቀፋ ተጠብቆ ይኑር። ያ የሚጠራችሁ ታማኝ ስለ ሆነ ይህን ያደርገዋል።
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:8-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos