ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ። ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ። ራሱ የሰላም አምላክ በሁሉ ነገር ይቀድሳችሁ፤ መንፈሳችሁ፥ ነፍሳችሁ፥ አካላችሁ በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚመጣበት ቀን ያለ ነቀፋ ተጠብቆ ይኑር። ያ የሚጠራችሁ ታማኝ ስለ ሆነ ይህን ያደርገዋል። ወንድሞች ሆይ! ለእኛም ጸልዩልን። ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ መሳሳም ሰላም በሉአቸው። ይህ መልእክት ለአማኞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ ስም ዐደራ እላችኋለሁ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:21-28
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos