ወንድሞች ሆይ! “ሰነፎችን ገሥጹ፤ ፈሪዎችን አደፋፍሩ፤ ደካሞችን እርዱ፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ” ብለን እንመክራችኋለን። ማንም ሰው በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ይልቅስ ሁልጊዜ እናንተ ለእርስ በርሳችሁም ሆነ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም ለማድረግ ትጉ። ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ባለማቋረጥ ጸልዩ፤ በሁሉ ነገር እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ሕይወት እግዚአብሔር ከእናንተ የሚፈልገው ይህን ነው። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ አታዳፍኑ፤ የትንቢትን ስጦታ አትናቁ፤ ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ። ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ። ራሱ የሰላም አምላክ በሁሉ ነገር ይቀድሳችሁ፤ መንፈሳችሁ፥ ነፍሳችሁ፥ አካላችሁ በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚመጣበት ቀን ያለ ነቀፋ ተጠብቆ ይኑር። ያ የሚጠራችሁ ታማኝ ስለ ሆነ ይህን ያደርገዋል። ወንድሞች ሆይ! ለእኛም ጸልዩልን። ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ መሳሳም ሰላም በሉአቸው። ይህ መልእክት ለአማኞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ ስም ዐደራ እላችኋለሁ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:14-28
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች