ወንድሞች ሆይ! ይህ ነገር ስለሚሆንበት ዘመንና ስለ ጊዜው ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልግም። የጌታ ቀን የሚመጣው፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ ዐይነት መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ደኅና አድርጋችሁ ታውቃላችሁ። ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም። እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፥ በጨለማ ውስጥ አይደላችሁም፤ ስለዚህ ቀኑ እንደ ሌባ አይመጣባችሁም። እናንተ ሁላችሁም የብርሃን ሰዎች፥ የቀንም ሰዎች ናችሁ፤ እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ሰዎች አይደለንም። ስለዚህ እኛ እንንቃ፤ ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር እንጂ እንደ ሌሎቹ አናንቀላፋ። የሚያንቀላፉ ሰዎች በሌሊት ያንቀላፋሉ፤ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉ። እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤ እግዚአብሔር የጠራን ለቊጣ ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት መዳንን እንድናገኝ ነው። ክርስቶስ ስለ እኛ የሞተው በሕይወት ብንሆን ወይም ብንሞት ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው። ስለዚህ አሁን በምታደርጉት ዐይነት አንዱ ሌላውን በማነጽ ያበረታታው።
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos